መ : መለስና መታደስ
Overview
አሁን ባለንበት ዘመን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመድረስ ጂ.ፒ.ኤስ (GPS) እንጠቀማለን። ጂ.ፒ.ኤስ ሳተላይትን የሚጠቀም ቴክኖሎጂ ሲሆን፣ ከአንድ መልክዓ ምድር ወደ ሌላ መልክዓ ምድር ለመድረስ ተመራጭና አቋራጭ መንገዶችን እየመራ የሚያደርስ ነው። መንፈሳዊ ሕይወታችንም ወደ መዳረሻው ማምራት ያለበት የጉዞ እንቅስቃሴ ነው። የምንሄድበትን መዳረሻ ካላወቅን፣ ጂ.ፒ.ኤስ ልንጠቀም አንችልም። ጂ.ፒ.ኤስ ጥቅም የሚሰጠን መዳረሻችንን ካወቅን ነው። መዳረሻችንን ካላወቅን፣ ጂ.ፒ.ኤስ ሊመራን አይችልም። ስለዚህ፣ ጂ.ፒ.ኤስ ስንጠቀም ሦስት ቦታዎች አሉ፦ ያለንበት፣ የምናልፍበትና የምንደርስበት።
ይህ መጽሐፍ በእነዚህ ሦስት ጽንሰ ሐሳቦች ላይ የተገነባ ነው፦ ያለንበት፣ የምናልፍበትና የምንደርስበት። መንፈሳዊ ሕይወታችን መዳረሻ (destiny) አለው። ነገር ግን ወደዚህ መዳረሻ መድረስ የምንችለው አሁን ያለንበትን ካወቅንና ወደ መዳረሻችን ለመድረስ መከተል ያለብንን መንገድ ስናውቅ ነው። ችግራችን መዳረሻችንን አለማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ አሁን ያለንበትን በቅጡ ላንረዳው እንችላለን። እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ያለንበትንም ሆነ የምንደርስበትን ያሳየናል። ያለንበትንና የምንደርስበትን ማሳየት ብቻ ሳይሆን፣ ካለንበት ተነሥተን ወደ መዳረሻችን የሚወስደንንም መንገድ ያሳየናል። ስለዚህ፣ መንፈሳዊ ጉዞአችን የተሳካ እንዲሆን ያለንበትን፣ የምናልፍበትንና የምንደርስበትን ማወቅ ይገባናል።
This item is Non-Returnable
Customers Also Bought
Details
- ISBN-13: 9781087882093
- ISBN-10: 1087882095
- Publisher: Ermias Woldeyesus
- Publish Date: October 2016
- Dimensions: 8 x 5 x 0.33 inches
- Shipping Weight: 0.35 pounds
- Page Count: 152
Related Categories
